Leave a reply

Enter your message below:

Visit our Social Media pages
Subscribe to
get updates

Entertainment

ኢትዮጵያን በበጋ! ዋው!

Best of Ethiopia to explore this Summer Season
ሞቅ ሲል፣ ምድሯ በዘላለማዊ አረንጓዴ ሳሮች፣ደኖች እና ባለ ብዙ ቀለማት አበቦች ሲሸፈን በረጅም ታሪኳ እና ዘርፈ ብዙ ባህሎቿ ወደ አሸበረቀችው ኢትዮጵያ ለመምጣት በመወሰናችሁ ፍፁም ደስተኛ እንደምትሆኑ ቅንጣት አትጠራጠሩ። አስደማሚው መልክዐ ምድሯ፣ ድንቅ አረንጓዴ ኮረብቶቿ፣ ወንዞቿ፣ ተራሮቿ፣ ፏፏቴዎቿ፣ ሸለቆዎቿ፣ ስነ ህንፃዎቿ፣ ጥብቅ ፓርኮቿ እና ብርቅዬ እንስሶቿ ጨርሶ በሕይወታችሁ ሁሉ ልትረሱት የማትችሉት እርካታ እና ትዝታ ነው የሚሰጣችሁ።
በእነዚህ መሳጭ የኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎች መጓዝ ይህ ቀረሽ የሚባል ነገር የለውም። በምትጓዙበት ሁሉ የዱር እንስሳት፣ ወፎች፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ እና ታሪካዊ ትዕይንቶች ብቻ አይደሉም ልባችሁን የሚገዙት በየመዳረሻዎቹ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፈገግታ እና ልባዊ አቀባበል ጭምር ነው። ያለ ምንም ጥርጥር ለማንም አስደማሚ እና መሳጭ ጉዞን ለማድረግ ለሚመኝ ሁሉ ኢትዮጵያን ማሰስ በህይወቴ ባያቸው ብሎ ከሚመኛቸው ድንቃ ድንቆች አንድም የሚጎልበት አይኖርም።
ተዘርዝረው የማያልቁ የዱር እንስሳት እንደ አዞዎች፣ ባለ መስመር ጎሾች፣ አቦሸማኔዎች፣ ዝሆኖች፣ ቀጭኔዎች፣ ጉማሬዎች፣ የሜዳ አህዮች፣ ሳላዎች፣ ኢንሹዎች፣ ከርከሮዎች፣ ሚዳቆዎች፣ ጓደኛ የሚያደርጓችሁ ጦጣዎች፣ ዝንጀሮዎች የትም የማቷገኟቸው ብርቅዬዎቹ ዋልያ አይቤክስ፣ የኢትዮጵያ ቀበሮ እና ጭላዳ ዝንጀሮን ጨምሮ ለቁጥር የሚያታክቱ የወፍ ዝርያዎች በበጋ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችሁ እንደሁ በቡረቃ ይቀበሏችኋል። በግምብ ወደ ታጠረችው የሙስሊሞች 4ኛ ቅዱስ ከተማ ሀረር ብቅ ያላችሁ እንደሆን ጅቦችን በእጃችሁ መመገብ ትችላላችሁ።
እነዚህ እና ያልጠቀስናቸው ውብ እንስሳት፣ በአረንጓዴው መስክ ላይ እንደ አበባ ተበትነው፣ በየትኛውም አቅጣጫ ብትሄዱ ከምታገኟቸው ወንዞች፣ የተፈጥሮ ፏፏቴዎች እና ምንጮች ስር ውሃ ሲጠጡ፣ ሰውነታቸውን ሲታጠቡ፣ ሲዋኙ አልያም ከትላልቆቹ ዛፎች ስር አረፍ ብለው ሲቆዝሙ ቀረብ ብሎ ማየት በትክክል ገነት የመግባት ያህል ፍሰሃ ይሰጣል። ንፁህ በሆኑት ሀይቆቿ እና ወንዞቿ መዋኘት ብቻ አይደለም፣ እድሜ ልካችሁን ልታወሩት የምትችሉት፣ አካላችሁን ዘና አድርጎ ነፍሳችሁን በሀሴት የሚሞላ ስሜት ማግኘት ከፈለጋችሁ፤ በተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች ተሞልተው ከውስጧ የሚፈልቁ ሙቅ የሆኑ ምንጮቿ ውስጥ መነከር ሲልም መዋኘት ትችላላችሁ።
የነፍሳችሁን እርካታ የምታገኙት ተራሮች አናት ላይ ቆማችሁ ቁልቁል ስትመለከቱ ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታችሁ አሁንም ፍፁም ትክክለኛ ውሳኔ ነው። የኢትዮጵያ ትንግርት ማለቂያ የለውም። በዓለማችን በሙቀቱ ተወዳዳሪ የሌለው ቦታ ለማየት እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ወዳለው ዳሎል መሄድ በቂያችሁ ነው። እግረ መንገዳችሁን የተፈጥሮን አስደናቂ ከስተት የኤርታሌን የእሳት ባህር በመጎብኘት ለልጅ ልጆቻችሁ የምትነግሩት እፁብ ድንቅ ትንግርት ታያላችሁ። ለዚህ ነው በበጋ ኢትዮጵያን መጎብኘታችሁ ዋው የሚያሰኘው። የአፍሪካ ጣራ ላይ ለመውጣት፣ በአህጉሩ ረጅሙን አረንጓዴ ተራራ የሰሜን ተራራ፣ በአፍሪካ በርዝመቱ 4ኛ የሆነውን የራስ ዳሽን ተራራ፣ የአቡነ ዮሴፍን ተራራ፣ የቱሉ ዲምቱ ተራራ፣ የጉና ተራራ እና የባሌን ተራሮች በመውጣት ለራሳችሁ ልዩ ስጦታ ለማበርከት በበጋ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ብቸኛው አማራጭ ነው።
ምርጫችሁ በደኖች ውስጥ መንሸራሸር እና ተፈጥሮን ማድነቅ ከሆነ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ኦሞ፣ ያቤሎ፣ ማንጎ፣ ነጭ ሳር፣ አዋሽ እና ያንጉዲ ራሳ ግዙፍ እና አረንጓዴ ብሔራዊ ፓርኮቿ፣ በድንቅዬ የዱር እንስሳት እና ባልተነካካ ተፈጥሮአቸው የማይሰጧችሁ ደስታ አይኖርም። ምንም በማያጠራጥር ሁኔታ ድፍን ኢትዮጵያ በሚያፈዙ እና ትንፋሽ በሚያሳጥሩ የተፈጥሮ ድንቃ ድንቆች የተሞላች ናት። በጋ የኢትዮጵያውያን ልዩ ምልክት ከሆነው አደይ አበባ ጀምሮ ምድርዋ፣ አትክልት ቦታዎቿ፣ ፓርኮቿ፣ በአጠቃላይ በአበቦች የተፈጥሮ ቀለማት የሚያሸበርቅበት በመሆኑ ጉዞአችሁን የማይረሳ ያደርገዋል። እውነት እውነት እላችኋለሁ በበጋ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ማለት፣ የሰው ልጅ መገኛ በመሆኗ ወደ ስረ መሰረታችሁ፣ ወደ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ወደ ልዩ እና ድንቅ ባህሎች መምጣት ማለት ነው።
ደርሳችሁበት ከማታውቁት የደስታ ማማ ላይ ለመውጣት እንዲህ ማድረግ ብቻ ነው የምትችሉት። እረፍታችሁን ውሰዱ፣ የመንገድ ጓዛችሁን ጠቅልሉ፣ በጋው ሳያልፍ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ብረሩ።
Enclosed in evergreen grasses, forest and colorful flowers, history and culture; coming to Ethiopia at this summer season offers the best time of a lifetime. Ethiopia is full of stunning landscapes and wildlife’s. From the incredible green hills, mountains, waterfalls and rock hewn architectures, the parks has unforgettable charm that will stay with you forever. The level of great adventure you get in Ethiopia will take you a whole new magnificent experience.
The stunning destinations in Ethiopia are not short of anything having so much of adventures options. From the historical destinations to the parks and the wild lives this breathtaking destination is truly a destination for everyone. For anyone searching for exciting travel, trying to create a memory that will last for life time, then here is Ethiopia’s best offers that standout everything you might have in your bucket list. Crocodiles, cape buffalos, lions, leopards, elephants, giraffes, hippos, zebras, over 20,000 birds and friendly monkeys are few of the wild lives you spot at the parks. Ethiopia is also home to several historical destinations. In Ethiopia there are plenty of waterfalls and natural springs where you can soak and dip into the natural hot waters. Whether you prefer to swim at the lakes or you want to relax at the warmest natural hot springs or you just want to watch the wildlife’s, be prepared for an exciting and amazing adventure that you will talk about for the years to come. Ethiopia has several spectacular lakes and lodges making every travel around Ethiopia unforgettable and life changing to the better.
If you are up to daring adventure and hiking you come to the right place. Head to the bubbling fire lake at Erta Ale and visit the hottest place of the planet at Dallol to taste your limits and to watch bliss of the incredible nature. Climb up the continent’s tallest green mountains at Semien Mountain which also known as roof of Africa. Ethiopia also offers daring and enormously rewarding trekking routes at Ras Dashen, Mount Abuna Yosef, Mount Tullu Dimtu, Mount Abuna Yosef, Mount Bwahit and Mount Guna. The greener parks are full of rare wild lives and forests and natural features preserved in their natural status. Head to Chebera Churchura National Park, Omo Park, Yabelo National Park, Mago National Park, Arba Minch and Nechisar National Park and Yangudi Rassa National Park are few of the best parks that are a must see in a lifetime.
There are plenty of breath-taking sights all around Ethiopia. If you are visiting during the summer seasons you are in great luck as it’s a time where the outdoor gardens flourishes and the scenic falls to its fullest ever green while the flowers bloom. A trip to Ethiopia’s is nothing like you experience anywhere in the world. It’s a trip that takes you deep into the beginning of civilization, history and exclusive culture. Being home to over ten UNESCO registered natural heritages. From ancient luxurious palaces, obelisks, rock hewn churches which will never go out of season. Take your vacation at this glorious destination at this summer for the ultimate adventure time.


Previous Posts:Subscribe to get updates

IN Pictures

Football Video Highlight

Entertainment