Leave a reply

Enter your message below:

Visit our Social Media pages
Subscribe to
get updates

Entertainment

ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር ካላችሁ

Full of natural wealth and ancient treasures in Ethiopia
ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር ካላችሁ …
ብዙዎች ኢትዮጵያ የተፈጥሮ እና ታሪካዊ ሀብቷን በበቂ ሁኔታ አልተጠቀመችበትም ይላሉ። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ ፊታችሁን ወደ ፈለጋችሁት አቅጣጫ ብታዞሩ፣ አስደናቂ የተፈጥሮ ፣ ሰው ሰራሽ እና ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎች ታገኛላችሁና ነው። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ውበትዋ፣ እና ጥንታዊ ታሪክዋ አለምን ዞረን አዳርሰናል የሚሉ ተጓዦችን አንኳ ቀልብ የሚስብ ነው። ነፍስን በሐሴት የሚሞላው የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ጨርሶ ሊዘሉት የማይገባ የተፈጥሮ ውበት ነው። ፍፁም እርካታን የምታገኙበትን ጉዞ ካሰባችሁ ጥንታዊቷን እና ታሪካዊዋን ኢትዮጵያን ለማሰስ መወሰናችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። በተፈጥሮ ሰማይ ጠቀስ እና አረንጓዴ ተራሮችዋ፣ ታሪካዊዎቹ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያኖችዋ፣ አስደናቂ ጥንታዊ ሀውልቶችዋ እና የትም የማይገኙ የዱር እንስሳትዎችዋ ኢትዮጵያ ለማንኛውም ተጓዥ መጨረሻ የሌለው እና ፍፁም እርካታን ለመጎናፀፍ ለሚፈልጉ ተጓዦች የምትመረጥ ሀገር ናት።
በዓለም እጅግ አስደናቂ ከሆነው ቀጥ ያለውን አቀበት፣ ጥልቅ ሸለቆ እና ዥው ያለ ገደል ካለው ከሰሜን ተራራ እንጀምር እስቲ። ይህ በኢትዮጵያ ካሉ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ የሆነው ተራራ፣ ተራራ መውጣት ፍፁም ለህይወታቸው ደስታ ለሚሰጣቸው ተጓዦች ፈፅሞ ሊዘሉት የማይገባ ቦታ ነው። ጨርሶ በሌላ ቦታ በማይገኙ እንስሳቱ እና እፅዋቶቹ የሚታወቀው እና በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ፓርክም ነው። በዚህ ተራራ አቦ ሸማኔ፣ ቀበሮ፣ ጅብ፣ ዲክዲክ የመሳሰሉ እንስሳት እና ከ400 በላይ የወፍ ዝርያዎች ይገኙበታል። ተራራ ከመውጣቱ በተጨማሪ እንስሳትን እና ወፎችን ማየት የሚያስደስታችሁ ከሆነ ይህ ቦታ እጥፍ ድርብ ደስታ ይሰጣችኋል። ይህ አስደናቂ እና አረንጓዴ መልክዓ ምድር ከተራራው አናት ላይ እየተወረወረ የሚወርድ አስደሳች የተፈጥሮ ፏፏቴም አለው። 4550 ሜትር ከፍታ ያለውን ተራራ ወጥታችሁ በቃን ማለት አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። በቀጥታ ከአፍሪካ ግዙፍ ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ራስ ዳሽን ተራራ ማምራት ነው የሚኖርባችሁ።
ራስ ዳሽን ተራራ በተለይ የዱር እንስሳትን ለማየት እጅግ ተመራጩ ቦታ ነው። ብርቅዬዎቹን ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ዋልያ አይቤክስ፣ እና የኢትዮጵያን ቀበሮ እዚሁ ተራራ ላይ ነው የምታገኟቸው። ውብ የቢራቢሮ ዝርያዎች፣ አስገራሚ ወፎች ለተራራው ተጨማሪ ውበትን የሚያጎናፅፉት ሀብቶቹ ናቸው። ራስ ዳሽንን መውጣት ማለት የተፈጥሮን ውበት ገደብ የለሽ በሆነ መጠን ማየት፣ ማድነቅ እና መደነቅን ስለሚፈጥር በህይወታችሁ ልትረሱት የማትችሉት ትዝታ ታገኛላችሁ። ወደ ኢትዮጵያ ከመጣችሁ ለማረፍ ጊዜ አይኖራችሁም፣ ምክንያቱም ኢትዮጵያ እጅግ ጥንታዊ እና ታሪካዊ በሆኑ መዳረሻዎች የተሞላች ናትና ነው። ገዳማቶቿ፣ ቤተ መንግስቶችዋ፣ ዋሻዎቿ እና የተፈጥሮ ሀብቶቿ እጅግ ያስደምማሉ።
የዝነኞቹ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያኖቿ ስነህንፃ ጥበብ ብቻውን አንኳ ወደ ኢትዮጵያ እንድትመጡ በቂ ምክንያት ሊሆን የሚችል ነው። እነዚህ በአስገራሚ የስነፅንፃ ጥበብ ከስምንት ክፍለ ዘመን በፊት ምንም ተጨማሪ የግንባታ ግብዓቶች ሳያስፈልጉ ከአንድ ድንጋይ ብቻ ተፈልፍለው የተሰሩ አስራ አንድ አብያተ ክርስቲያናት በአለማችን በየትኛውም ክፍል ተሰርተው የማያውቁ ልዩ የኢትዮጵያውያን የጥበብ ውጤቶች ናቸው። ጎንደር ላይ አፄ ፋሲል በ 17ኛው ክፍለ ዘመን ያስገነቡት 70 ሺኅ ስኩር ሜትር አረንጓዴ መልክዓ ምድር እና በዩኔስኮ የዓለም ሀብትነት የተመዘገበው 8 ህንፃዎች፣ የነገስታቱ መኖሪያ ቤት እና የአምልኮ ስፍራን ጨምሮ ያለው ቤተ መንግስት ሌላው አስደማሚ እና ሊትጎበኙት የሚገባ ነው።
በ4ኛው ክፍለ ዘመን በሚያስደንቅ ጥበብ የቆመዉን የአክሱም ሀውልት ሳትጎበኙ መመለስ ጉዟችሁን ሁሉ ጎዶሎ ያደርግባችኋል። እጅግ ግዙፍ የሆነው እና 82 ጫማ ርዝመት ያለው ከአንድ ወጥ ግራናይት፣ ድንጋይ ተጠርቦ የተተከለ ሀውልት ነው። ከአጠገቡ 108 ጫማ ርዝመት የነበረው ተመሳሳይ ሀውልት መሬት ላይ ወድቆ ስለምታገኙ ቀረብ ብላችሁ ስለዚህ ሀውልት ጥበባዊ እና ሚስጥራዊ አሰራር መመርመር ትችላላችሁ። ይህ ሀውልት እስከዛሬ እንደቆመ ቆይቶ ቢሆን ኖሮ ከአለማችን ረዥሙ ሀውልት ይሆን ነበር። ገና ሰሜን ኢትዮጵያን አልጨረሳችሁም። ስለ ኤርታሌ አስደናቂነት ሰምታችሁ ወደ ኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምዕራብ ጫፍ መጓዛችሁን ፈፅሞ ማቆም አትችሉም።
ኤርታሌ በአለም ላይ ካሉ አምስት ወደር የሌላቸው ድንቅ ክስተቶች አንዱ የሚንተከተክ እሳተ ጎሞራ የሚገኝበት በአፋር ክልላዊ መንግስት የሚገኝ ቦታ ነው። የኤርታሌ የእሳተ ጎሞራ ባህር በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ ነው። ይህ የሚንተከተክ እሳት 2011 ጫማ የእሳት ወደብ አለው። ይህ የእሳት ተራራ በሚንተከተከው እሳቱ ሳቢያ “የገሀነም መውጫ” በመባል ይታወቃል። ፍፁም ማራኪ የሆነው ቦታ ከአናቱ ላይ እሳት ቢንተከተክም ሊጎበኝ የሚችል እንዲያውም እስከ ተወሰነ ደረጃ ጠጋ ብለው ሊመለከቱት የሚቻል ስፍራ ነው። ወርቀማ መልክ ያላቸው የሚንተከተኩት አለቶች በተለይ በምሽት እጅግ መሳጭ ትዕይንቶች ናቸው። በመሬት ላይ የራሱን ሸለቆ ሰርቶ የሚፈሰው የእሳት ባህር ፍፁም አቻ የሌለው ትዕይንት ነው።
ከዚህ ሞቃታማ ቦታ ወጥቶ መንፈስን የሚማርክ የሀይቆች ዳርቻ ጉዞ ለማድረግ ኢትዮጵያ አሁንም አማራጮች አሏት። በሐይቆቹ ውሃ ለመነከር፣ ለመዋኘት ወይም በሐይቆቹ ላይ እየተነሽራሸሩ የአካባቢውን ውበት ለማድነቅ እና ለመመሰጥ ከተመኛችሁ ወደ እነዚህ ሐይቆች ፍጠኑ። ፍፁም ንፁህ እና በተፈጥሮ ሀብቶች ወደ ሞሉት ወደ እነዚህ ሐይቆች ፍጠኑ። ጣና፣ ቢሾፍቱ፣ ሆራ፣ ኪሎሊ፣ ኩሪፍቱ፣ ላንጋኖ፣ ሻላ፣ አባያታ፣ ሀዋሳ እና በአድናቆት አፍ የሚያስከፍቱትን አርባ ምንጭ በተፈጥሮ ድልድይ የሚገናኙት የጫሞ እና አባያ ሀይቆች አይተው የማያውቁትን የመንፈስ እርካታ ከሚያገኙባቸው ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ ሐይቆች ዳርቻ ቡኒው አሸዋ ላይ ተንጋላችሁ ህይወትን እያጣጣማችሁ በኢትዮጵያ ስላሳለፋችኋቸው አስገራሚ የጉዞ ታሪኮች ማሰላሰል ትችላላችሁ።
Fabulous Ethiopian destinations you should never skip
Full of natural wealth and ancient treasures made Ethiopia glamorous country enticing even seasoned travelers who has seen most parts of the world. Explore the ancient historical country for an absolute inspiring adventure. The scenery of magnificent Ethiopian destinations are never to be missed. From the rock hewn churches to obelisks to sky rise green mountains, Ethiopia offers endless and unforgettable escapades that certainly fulfils your dream of perfect adventure. Start with Simian Mountain the gigantic landscape with one of the world’s most stunning sharp mountain peaks, deep valleys and sharp precipices. It’s one of the rare locations in Ethiopia and a must see place to those who love trekking coupled with so much adventures. It’s a UNESCO registered park for its vastly wide range of rare wildlife and vegetation. Several wildlife’s to the mountain including Leopard, klipspringer, bushbuck, Jackal and hyena and over 400 species birds inhibit the mountain park creating multiple adventure opportunities for those who love trekking and wildlife view. The massive green landscape also includes long waterfall flowing from the upper part of the mountain gashing to the ground. Hike up to a rewarding trekking journey up in the top of the mountain at 4,550 meters above sea level. Do not just stop there rather head to Ras Dashen Mountain it is the best spot for trekking and wildlife spotting. Explore so much fun and exciting nature extravaganzas that will stay in your mind for a lifetime. Climb up at the green massive Mountain to admire the wild animals including gelada baboon, walia ibex and Ethiopian wolf. The mountain sanctuary is full of birds and butterflies who add exceptional colour and beauty to the place.
Don't even think about giving your neck a rest for a second, the spectacular destinations are endless and breathtaking. Ethiopia is famous for its historical sanctuaries, temples, palaces and stunning natural creations. Step into this paradise a natural extravaganza where you witness the country’s rare and breath-taking destinations. From palaces to obelisks and rock hewn churches, it has an amazing ancient architecture. The famous rock hewn Lalibela churches are a significant place of pilgrimage and pride being the Ethiopian iconic structures. The UNESCO registered global heritage is the most outstanding design ever built in the country. It has eleven monolithic and semi-monolithic structures that were built by carving a single huge rock eight centuries before without adding any external building materials like bricks and cement. Nearby there is a spectacular palace Fasilides built in the 17th century. Lying in massive 70,000 square meter green landscape the UNESCO World Heritage castle contains eight properties home for the royals including a temple where they used to worship in their royal congregation.
Do not just stop, there is a lot more to discover in Aksum. The strong standing obelisks were erected back in the 4th century. The enormous monuments made from a single piece of granite of smooth gray stone stand as high as 82 feet. Another 108 feet long Aksum obelisk lies shattered across the ground allowing a close up view of the magnificent rock formation. If it were still standing it would have been the tallest obelisk in the world. The obelisks resemble buildings with intricately carved cross-shaped windows, and rows of long ends dividing each story artistically.
Do not miss out on Ethiopia’s extreme locations as it takes adventure to the next level. Erta Ale one of the five global extreme wonders with active bubbling volcano lies at the North-eastern part of Ethiopia famously known as Afar Regional State. It existed since the beginning of the 20th century. The stunner fire sea floor bubblies 2,011-feet with a fire shore. The fire mountain is known as “the gateway to hell” due to the active fire floor. It’s the most amazing natural feature. Although there is active volcano bubbling to the top it’s perfectly safe to visit and even take a closer look to the fire lake. The golden sparkling molten rock has an awe-inspiring view especially during the nights. The flow of lava from deep in the ground creating a river of liquid fire is truly an matchless view.
Finally head to the lakes to have an inspiring lake adventure. Sock up to the lakes swimming or cruise to the middle of the lakes enjoying the surrounding view. Escape to the refreshing lakes where you will have an unforgettable experience. Discover the stunning paradise at the crystal clear full of marine life lakes. Lake Tana, Bishoftu, Lake Hora Kiloli, kuriftu, Hora, Langano, Lake Shala, Abyata are the major lakes where you can have an uncommon adventure. Lie-down at the brown sands enjoying and counting down your Ethiopian adventure.
Article by Eden Sahle


Previous Posts:Subscribe to get updates

IN Pictures

Football Video Highlight

Entertainment