Leave a reply

Enter your message below:

Visit our Social Media pages
Subscribe to
get updates

Entertainment

ጉራጌዎች እና ማራኪው አካባቢያቸው

Bites and sights of the Stunning Gurage
ጉራጌ የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያን ለጥቂት ቀናት ጎብኝቶ የተመለሰ የውጭ ዜጋ ጭምር ወዲያው በአዕምሮው ብልጭ የሚሉ ነገሮች አሉ። በባህርይ ታታሪ፣ ፈጣን፣ ጠንካራ እና የስራን ክብር ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ። መልካም ጎረቤት፣ ሰው አፍቃሪ እና መተጋገዝ የማደግ መሰረት መሆኑን አብጠርጥሮ የተረዳ ህዝብ፤ በአመጋገብ በዛ ልዩ ክትፎ፣ ቆጮ ፣ አይቤ እና ጎመን፣ ቡላ፣ ቅቤው ሳይረሳ፥ ስለ ተፈጥሮ ካለን ደግሞ ውብ እና ማለቂያ የሌለው አረንጓዴ መሬት እና ራቅ ራቅ ብለው ለውበቱ ድምቀት የሚጨምሩለት፣ በእንሰት ተክሎች የተከበቡ የጉራጌ ጎጆዎች፣ ከዛም በላይ ደግሞ በተለይ በልዩ ሁኔታ ከአንድ ባለ ሁለት ጡት ጀበና እንደየ ምርጫ የሚንቆረቆረው ልዩ የጉራጌ ቡና በቅቤ እና ቡና በጨው።
ዛሬ የህይወት አመለካከት እየተለወጠ፣ ወጣ ብሎ መመለስ ባህል እየሆነ በመጣበት ጊዜ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለአለም አቀፍ ጎብኝዎች አንድ እርካታን የሚያገኙበት የጉዞ አማራጭ ነው የጉራጌ ዞን። ከተማው ችክ ሲልቦት፣ አካልዎ በስራ ሲዝል እና መንፈስዎ ሲወጠር ወጣ ብለው ታይቶ በማይጠገበው አረንጓዴ መልክኣ ምድር መሀከል በንፁህና ውብ የኮባ ተክል በተከበቡ የጉራጌ ጎጆዎች የተመሰሩቱ መንደሮች ውስጥ ከእንግዳ ወዳዱ የጉራጌ ህዝብ መሀል አረፍ ብለው መመለስ እንደገና እንደ መወለድ ያህል ነው።
ወደ ጉራጌ ህዝብ መሀል ሲሄዱ ቀልቦን የሚገዛው ባህሉ፣ ገበያው ውስጥ የሚያዩት በቀለማት ያሸበረቀ ውበት፣ ሐይቁ፣ ዋሻዎቹ ብቻ አይፈሉም፣ ልቦዎን በሃሴት የሚሞላው እና ዘላለማዊ ትዝታን የሚሰጥዎት ከልጅ እስከ አዋቂ በሚያልፉባቸው መንደሮች ሁሉ የሚቀበሎት የጉራጌ ህዝብ እጆቹን እያውለበለበ የሚሰጥዎት ፈገግታ እና ፍቅር ነው።
ሲፈልጉ ለታላቁ ስምጥ ሸለቆ ቀረብ ወደ ሚለው ቡታጅራ ጎራ ማለት ይችላሉ። ጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ ሩቅ አይደለም። ወልቂጤ ከአዲስ አበባ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ነው። በአውቶብስ ቢጓዙ በሶስት ሰዓታት ውስጥ ራስዎን ከመሀል ከተማው ያገኙታል። የጉራጌን አርሶ አደር ህይወት ለመቃኘት፣ አይን የሚያፈዘውን አረንጓዴ መልክዓ ምድር ያለስስት ለመኮምኮም፣ የጉራጌ ተራራ ቀዝቀዝ ካለው እና ህይወትን ሀሴት ከሚሞላው አየሩ ጋር አማራጭ የሌለው አማካይ ስፍራ ነው።
በአቅራቢያው የሚገኘው ዋሻ እና ሀይቆቹን መጎብኘት ለብዙዎች እጅግ ማራኪ እና የሚያዝናና የጉዞ መዳረሻ ሆኖላቸዋል። የጉራጌን አስገራሚ ተፈጥሮ፣ ለጥ ያሉ ሜዳዎች፣ ወጣ ገባ ኮረብታዎች፣ ፍፁም መንፈስን የሚገዛ ውብ ደን፣ ሸለቆዎች፣ ወንዞች፣ ፏፏቴዎች ሁሉንም አንድ ቦታ ሆነው ሊመሰጡባቸው፣ ሊዝናኑባቸው ልብዎ ከፈቀደ የጉራጌ ተራራን መውጣት ብቻ በቂ ነው።
ከተራራው አናት ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት ተራራው አናት ላይ ሲወጡ እና ከአካባቢው አሻግረው ሲመለከቱ ትንፋሽ የሚያሳጥረው የታላቁ የስምጥ ሸለቆ እይታ እና ሌሎችም ማራኪ ውበቶች ተራራውን ለመውጣት የደከሙት ድካምዎን ኢምንት ያደርግቦታል። የጉራጌ ዞን ከአዋሽ እና ከኦሞ ወንዞችም ጋር ወሰንተኛ ነው። ወደ ዋሻዎቹ ጎራ ብትሉ ውስጡን መኖሪያ አድርገው የተቀመጡ የጉራጌ ቤተሰቦች ታገኛላችሁ።
አደራችሁን ወደ ጉራጌ ዞን ጎራ ካላችሁ ካለምንም ማዳበርያ የበቀሉ የእርሻ ውጤቶቸን ልትሸምቱ የምትችሉበትን ትልቁን የጉራጌ ገበያ ውህጀባርን ሳታዩ እንዳትመለሱ። ይህ ማለት ደግሞ ገበያው ወደ ሚቆምበት ወደ ጉራጌ ተራራ ወጣችሁ ማለት ነው። ይህን በማድረጋችሁ ደግሞ ከላይ የነገርናችሁን አይንን እና መንፈስን ሰቅዞ የሚይዘውን ተፈጥሮአዊ ውበት እና ፍፁም በቀለማት የሚያሸበርቀውን የጉራጌ ገበያ እና ገበያተኛ ውበት ከነፍሳችሁ ታዋህዳለችሁ ማለት ነው። ወደ ጉራጌ ዞን ለመሄድ ስትነሱ ምንም የሚያሳስባችሁ ነገር የለም። ህዝቡ ፍቅር ነው፣ ፈገግተኛ ሰላምተኛ በመሆኑ ባለፋችሁበት መንደር እና መንገድ ሁሉ እጁን እያውለበለበ የሚሰጣችሁ ሰላምታ ራሳችሁን እንደ ታዋቂ ግለሰብ እስክትቆጥሩት ድረስ ያስገርማችኋል። በጉራጌ ባህል እንግዳ ሁሉ ታዋቂ ግለሰብ ነውና። ከለመዳችኋቸው የጉራጌ የባህል ምግቦች፣ ክትፎ፣ ጎመን ክትፎ፣ አይብ፣ ዝማሞጃት፣ ቆጮ እና ቡላ በላይ የሚያስጎመጁ እና የሚጥሙ የምግብ አማራጮች ታገኛላችሁ። ቆጮ ብቻውን እንኳ ለቁጥር የሚታክት እጅ የሚያስቆረጥሙ ምግቦች ይዘጋጁበታል።
አዕምሮአችን በስራ ለረዥም ጊዜ ሲወጠር፣ አካላችን ሲዝል ወደ መጀመሪያው ጉልበታችን ለመመለስ አረፍ ማለት፣ ዘና ማለት ያስፈልገናል። ለዚህ ፍፁም መታደስ አማራጭ ከሚሆኑን ቦታዎች አንዱ እና ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ ሰብሰብ ብሎ ጎራ ብሎ ተዝናንቶ፣ ተደስቶ ሊመስበት ከሚችልባቸው መዳረሻዎች አንዱ የጉራጌ ዞን ነው።
ጎራ ብለን ከዚህ ሞልቶ ከሚፈስ ውበት እና ፍቅር ቆንጠር አድርገን ብንመለስ ለወራት አጠንክሮ የሚያሰራን ስንቃችንን ቋጠርን ማለት ነው።
Dubbed as one of the hardest working societies in Ethiopia, Gurage, located in Southern part of the country is a perfect place for nature buffs and to those who want to try amazing local dishes. It�s a place where people travel far for its incredible adventure and natural bliss. You will want to head to Gurage for its exciting nature, food and its organic salted coffee, culture and certainly for a lot more.
With the growing array of adventure and bites the place has become a darling for locals and foreign visitors. It�s a timeless destination which will keep you inspired and fulfilled. This deep green location with traditional villages and houses is where many go to escape the regular and the crowed of big cities. The place is glamorous and full of traditional people who wave and smile at you while you walk by their villages. Get outside and explore Gurage culture, market, Crater Lake and caves for everlasting delighting memory.
Start with Butajira and Welkite one of the awesome places of Gurage found on the road to Lake Ziway. It is located about 120 kilometres Southwest of Addis Ababa the capital city. From Addis Ababa a 3 hours comfortable bus ride will take you right in the middle of the great adventurous places. Butaijira located near the Great Rift Valley and mount Gurage is the central location to have the best of Gurage. Its green plains are to die for it�s full of refreshing weather, farms and best place to observe the local traditional life style. The crater lakes and the nearby cave which people use as home is a magnificent site to explore.
Hike up to the giant green mountain Gurage to explore the rugged and stunning terrains, villages, forests, canyons, and waterfalls. The top view is truly rewarding with its breathtaking view of the Great Rift Valley and the surrounding attractions. It forms part of the split dividing the drainage basins of the Awash and Omo rivers. Stop by at the cave where you will meet villagers who made the cave a warm home. The mountain also gives a great view of the lake, the massive canyon, the forests and the gorges. Do not miss out from Wuhjebar biggest market where you can purchase organic produce which are freshly cultivated for the market day. Wuhjebar is located on top of the mountain Gurage allowing you to enjoy the market and the site.
Gurage is truly a stunning place with lots of cheering activities and mouth-watering eatery. Uncover the delicious food tours at the place which made several exclusive local dishes at its best. The Gurage yummy cooking uses a rich array of locally fermented butter and homemade spices. The place is particularly famous for gomen (chopped collard greens), kitfo (minced raw beef), tibs (traditionally seasoned and fried meat), gord gored (cubed raw meat) with spices and ayibe (crumble cheese). Kocho the vegetable bread made from pulverized and fermented banana plant seed powder is very much worth tasting there is truly an absolute chance that you will not have enough if it. The plant bread is not only delicious but also nutritional prescribed by doctors for bone strength and repair. Kocho is not the only organic plant food here you can also have bulla the powdered plant root porridge which can be the best porridge you ever tasted. Complete your glamorous vacation with the organic coffee inside the traditional villages that will keep you warm and delighted.


Previous Posts:Subscribe to get updates

IN Pictures

Football Video Highlight

Entertainment